በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቃቂ ቃሊቲ  ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በሚገኘው ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በግምት ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

 እሳቱ ከቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ መነሳቱን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ባለስልጣን ሰራተኞች ፣ የፖሊስ አባላት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ እሳቱን ለማጥፋት በመረባረቡም ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡  
 
ወቅቱ ደረቃማና ነፈሻማ የአየር ሁኔታ ስለለው ለመሰል አደጋዎች ሊያጋልጥ ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡