የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በነገው እለት በባለሙያዎች ደረጃ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የ30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መንገዶችን የማስተካከል ስራዎች መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በመዲናዋ ለሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ እንግዶች የሚንቀሳቀሱባቸውን መንገዶች የመጠገን፣ ጽዱ የማድረግ፣ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችን የማዘጋጀት እና ተለዋጭ መንገዶችን የማስተካከል ስራዎች ማጠናቀቁን ገልጿል።

በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ አካባቢም ከ120 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ማዘጋጀቱን፥ የባለስልጣኑ የመንገዶች ጥገና ዳይሬክተር ኢንጅነር መኮንን ጥበቡ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የመገንድ ጥገና እና ማስዋብ ስራዎችን ለማከናወን ስድስት ቡድኖች መሰማራታቸውንም ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በነገው እለት በባለሙያዎች ደረጃ ይጀመራል።

 

በዙፋን ካሳሁን