የጥምቀት በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 11 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ በዓሉ በሰላም መከበሩን አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር የከተማዋ ነዋሪ በተለይ ደግሞ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጋቸውንም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ የፀጥታው ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አመለካካት በመያዝ፥ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውሷል።

ነዋሪው እያበረከተ ላለው ቀና ትብብር ምስጋናውን ያቀረበው ኮሚሽኑ፥ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡