ፕሬዚዳንት ሙላቱ ሁለት የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ኢትዮጵያን በውጭ ሃገራት ለሚወክሉ ሁለት አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ።

በዚህም መሰረት አቶ አባይ ወልዱ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።

መረጃውን ያደረሰን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ነው።