ኳታር ከግብፅ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ አለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኳታር ከግብፅ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን አል ታኒ፥ ሀገራቸው ከግብፅ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።

በኳታር እና በግብፅ መካከል ከ4 ዓመት በላይ የዘለቀውን አለመግባባት ለመፍታት ፈቃደኛ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ግብፅ ከ2011 ጀምሮ ከባድ ችግሮችን እንዳሳለፈች ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ ሀገሪቱ በአረቡ አለም ያላትን የመሪነት ሚና እንደሚያደንቁም ገልፀዋል።

ዶሃ በካይሮ የውስጥ ጉዳይ እንደማትገባም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በኳታር የሚደገፉት የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ሙርሲ በ2013 በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ መቀዛቀዙ ይነገራል።

ግብፅ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ባህሬን ሽብርተኝነትን ትደግፋለች ካሏት ኳታር ጋር የነበራቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጣቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ aa.com.tr