ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ለመተሳሰር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አቻቸው ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያዩ።

ዶክተር ወርቅነህ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ይፋዊ ግብኝት በማድረግ ላይ እያሉ ነው ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተገናኝተው የተወያዩት።

Workneh_UAE_2.jpg

ሁለቱ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ብዙ ያልተነኩ የትብብር መስኮች እንዳሉ አመልክተዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም የበለጠ ለማጎልበት ከመግባባት ደርሰዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በሀገራቱ መሀከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ተስማምተዋል።

ዶክተር፥ ወርቅነህ ኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የላትን ግንኙነት ትኩረት እንደሚትሰጥ ገልፃዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ያለ ህጋዊ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵዊን ዜጎች የሚሰሩበት ሁኔታ ዙሪያም ተወያይተዋል።

Workneh_UAE_3.jpg

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ባሳለፍነው ማክሰኞ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የገቡት ዶክተር ወርቅነህ በትናንትናው እለት ከሀገሪቱ ሰራተኛና የሰው ሃብት ሚኒስትር ናሲር ቢን ሀኒ አልሀሜሊ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህም በሁለቱ አገሮች የስራ ስምሪትን በተለመከተ የሰነድ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር በመጥቀስ ውይይቶቹን በማጠቃላል የመግባቢያ ስምምነት እንዲፈረም ተስማምተዋል።

የስምምነቱ መፈረም ኢትዮጵያውያን በህጋዊ መንገድ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ የመስራት ዕድል ይፈጥራል።

በተጨማሪም ሁለቱ ሚኒስትሮች ያለ ህጋዊ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ በአገሪቱ የሚኖሩ ዜጎች ዙሪያም መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ግንኙነት ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም ኢትዮጵያ ቆንስላዋን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2004 በዱባይ የከፈተች ሲሆን፥ ኤምባሲዋን ደግሞ በ2014 በአቡ ዳቢ ከፍታለች።

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2010 ነበር ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ የከፈተችው።

የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የንግድ ግንኙነት ከ10 ዓመት በፊት ከነበረበት 45 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ዶላር ባሳለፍነው የፈረንጆች 2016 ዓመት ከ809 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላርመብለጡን

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያስረዳል።