በአራቢያን ባህር በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ 13 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የካራቺ ከተማ ወደብ አቅራቢያ በሚገኘው አራቢያ ባህር፥ አንድ ጀልባ ሰጥማ በትንሹ 13 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

በደረሰው የመስጠም አደጋ የ20 ሰዎች ነፍስ ማዳን መቻሉ ተገልጿል።

ጀልባዋ ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ከ50 በላይ ተጓዦችን አሳፍራ ስትጓዝ ነበር አደጋው የደረሰው።

ከተነሳችበት ጣቢያ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ከተጓዘች በኋላ ባጋጠመው ከባድ ንፋስ ምክንያት ባህር ውስጥ መስጠሟ ተነግሯል።

መንገደኞቹ ከካራቺ ዋና ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ታታ ግዛት በሚከበር ክብረ በዓል ላይ ለመታደም እየተጓዙ እንደነበርም ተጠቁሟል።

የሲንድ ግዛት አስተዳደር ቃል አቀባይ፥ ሁለት ሴቶች እና ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 13 ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

የአካባቢው አስተዳደር የፍለጋ እና የነፍስ ማዳን እይተካሄዱ መሆኑን ቢገልፁም፥ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችለ ስጋት አለን ብሏል።

 

 

ምንጭ፦ http://aa.com.tr