የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በመጪው ቅዳሜ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ስምንተኛ መደበኛ ጉባኤውን ከመጪው ቅዳሜ ህዳር 16/2010ዓ.ም ጀምሮ በባህርዳር ከተማ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ አንደገለጹት፥ ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ጉባኤው የክልሉን ትምህርት ቢሮ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት በማዳመጥ ውይይት ያደርጋል።

በጉባኤው የጣና ሃይቅን በአደገኛ ሁኔታ የወረረውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት እና የወደፊት አቅጣጫዎችን እንደሚገመግሙ ገልጸዋል።

በሃይቁ ዙሪያ እየተስተዋለ ያለውን ብክለት በዘላቂነት ለማስወገድ በሚያስችሉ ስራዎች ዙሪያም ይመክራል" ብለዋል።

ምክር ቤቱ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በሩብ ዓመቱ በክልሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ያከናወናቸውን ተግባራት እንደሚገመግምም አቶ ይርሳው አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ዳኞችን ሹመት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

ምንጭ፦ኢዜአ