የአሜሪካ ባህር ሀይል አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ ደረሰበት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ባህር ሀይል አውሮፕላን በጃፓን ባህር ላይ የመከስከስ አደጋ ደርሶበታል።

በጃፓን ባህር ላይ የመከስከስ አደጋ የደረሰበት አውሮፕላኑ 11 የበረራ ሰራተኞች እና ሌሎች ተሳፋሪዎችንም ጭኖ እንደነበረ ተነግሯል።

አውሮፕላኑን ለአደጋ የዳረገው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም የተባለ ሲሆን፥ በበረራው ላይ ነበሩ ሰዎች ዝርዝር መረጃም እንደደረሰው ይፋ እንደሚያደርግ የአሜሪካ ባህር ሀይል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ዩ ኤስ ኤስ ሮናልድ ሬገን ወደ ተባለው የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በመጓዝ ላይ እያለ የመከስከስ አደጋው እንደደረሰበትም የባህር ሀይሉ አስታውቋል።

የአሜሪካ ባህር ሀይል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ አደጋዎች እያጋጠሙት ሲሆን፥ ባሳለፍነው ዓመት ነሃሴ ወር ዩ ኤስ ኤስ ጆን ማኬይን የተባለ መርከብ ሲንጋፖር አቅራቢያ ከታንከር ጋር በመጋጨቱ ምክንያት የ10 የባህር ሀየል አባላት ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

ከሁለት ወራት በፊትም ዩ ኤስ ኤስ ፊትዝጄራርደ የተባለው መርከብ ከእቃ ጫኝ መርከብ ላይ በመጋጨቱ የ7 የባህር ሀይሉ ህይወት ማለፉም አይዘነጋም።

ከዚህ በተጨማሪም ዩ ኤስ ኤስ አንቴይንታም በተባለው መርከብ ላይም ተመሳሳይ የመጋጨት አደጋ ደርሶ የነበረ ሲሆን፥ በግንቦት ወር ላይም ዩ ኤስ ኤስ ሌክ ቻምፕሌይን የተባለው መርከብ ከደቡብ ኮሪያ የአሳ አጥማጅ መርከብ ላር ተጋጭቷል።

ምንጭ፦ www.bbc.com