የኢራቅ ወታደሮች የኪርኩክ ከተማን ተቆጣጠሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢራቅ መንግስት ወታደሮች የኪርኩክ ከተማን መቆጣጠራቸው ተሰማ።

የኢራቅ መንግስት የኩርዲስታን ከፊል ራስ ገዝ አስተዳደር ከሶስት ሳምንት በፊት ከአራቅ ለመገንጠል ህዝበ ውሳኔ ማካሄዱን ተከትሎ አካሄዱን ሲቃወም ቆይቷል።

ህገ መንገስታዊ አይደለም ያለውን ህዝበ ውሳኔ ለመቀልበስም፥ አካባቢውን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው በሚል ጦሩን ወደ ከተማዋ አስገብቶ ነበር።

በዛሬው እለትም የመንግስት ወታደሮች ያለምንም ውጊያ ነዳጅ ማውጫ ስፍራዎችን ጨምሮ በርካታ ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥረናል ብለዋል።

የኢራቅ ጦር ከተማዋን መቆጣጠሩን ተከትሎም ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እየወጡ ነው ተብሏል።

ጦሩም ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ የኩርድ ሰንደቅ አላማዎችን አውርዷል ነው የተባለው።

ኪርኩክ በነዳጅ ዘይት የበለጸገችና በኩርዲስታን ግዛት ክልል ውስጥ የምትገኝ ከተማ ናት።

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ