ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት በአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ መሆኗ ተመለከተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2006 (ፍ.ቢ.ሲ.) ኢትዮጵያ ባለፉት ዓምሰት አመታት በአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ ሃገር መሆኗን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የ2014 የኢኮኖሚ ሪፖርት አመለከተ ።

 

በሪፖርቱ እንደተገለጸው ኢትዮጵያ እ.አ.አ ከ2009 እስከ 2013 ድረስ በአማካኝ የ9 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሃገሪቱ ይህንን የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበችውም ፤ በአገልግሎትና ኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እያከናወነቻቸው ባሉ ሰፊ ተግባራት ፤ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በኩል በተከናወኑ ውጤታማ ስራዎችና

በሌሎችም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ነው ብሏል ሪፖርቱ ።

ኢትዮጵያም  ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ትኩረት በመስጠቷ በቆዳ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገቧ በሪፖርቱ ወቅት ተጠቅሷል።

ይህንንም ወደ ሌሎች ዘርፎች ለማስፋፋት እየተጋች መሆኑን በኢንዱስትሪ ሚንስቴር የሚንስትር ድኤታ ልዩ አማካሪ አቶ አህመድ ኑር ተናግረዋል።

በሪፖርቱ ከኢትዮጵያ በመቀጠል የ8 ነጥብ 7 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ሁለተኛ ሆና የተቀመጠችው ሊቢያ ናት ።

ይህም በነዳጅ ሃበት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው የተመለከተው ።

በትዕግስት አብርሃም