በማሌዥያ በአንድ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ላይ በደሰረ የእሳት አደጋ በትንሹ 25 ሰዎች ሞተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሌዥያ ዋና ከተማ ኳላ ላምፑር በአንድ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ላይ በደሰረ የእሳት አደጋ በትንሹ 25 ሰዎች ሞተዋል።

እሳቱ በተህፊዝ ዳሩል የቁርዓን ትምህርት ቤት ነው የተከሰተው።

የእሳት አደጋው በተከሰተበት ወቅት ከመኖሪያ ክፍላቸው መስኮት በብረት የታጠረ መሆኑ ተማሪዎቹ እንዳያመልጡ በማድረግ ጉዳቱን እንዳባባሰው ተነግሯል።

አደጋው ከ20 ዓመት ወዲህ በጉዳት መጠኑ አስከፊው መሆኑ ነው የተነገረው።

እድሜያቸው ከ13 እስከ 17 የሚሆኑ 23 ወንድ ተማሪዎች በእሳት አደጋው ህይወታቸው ካለፉት ውስጥ ይገኛሉ።

ቀሪዎቹ ሁለቱ የትምህርት ቤቱ መምህራን ናቸው ብሏል የከተማዋ የእሳት አደጋ መቆጣጠር መስሪያ ቤት በሪፖርቱ።

የእሳት አደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው ተብሏል።

የኳላ ላምፑር ፖሊስ አዛዥ አማር ሲንግ በእሳት አደጋው የሞቱ ሰዎች አስክሬን ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎና ተነባበሮ መገኘቱን ተናግረዋል።

 

 

 

 


ምንጭ፦አልጀዚራ