አዲስ ለተሾሙት አምባሳደሮች ስልጠና መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ለተሾሙ 12 አምባሳደርነት ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአዳዲስ አምባሳደሮቹ ስልጠናውን መስጠት የጀመረው በውጭ ጉዳይና ሀገራዊ ደህንነት ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ነው።

በተጨማሪም አምባሳደሮቹ ወደተሾሙባቸው አገራት ሲሄዱ የሚያስፈልጋቸውን በድርድር፣ በኢኮኖሚ እና በህዝብ ዲፕሎማሲ ላይ ያላቸውን አቅም የሚያሳድግ ስልጠና እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በቅርቡ የተሾሙት፦

ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን - በአሜሪካ ዋሽንግተን
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ - በቻይና ቤጂንግ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አስቴር ማሞ - በካናዳ ኦታዋ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም - በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና - በስዊድን ስቶኮልም
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተበጀ በርኼ - በየተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ አቡ ዳቢ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ - በኳታር ዶሃ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ - በኢንዶኔዥያ ጃካርታ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሉሊት ዘውዴ - በሩዋንዳ ኪጋሊ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዓሊ ሱሌይማን - በፈረንሳይ ፓሪስ
ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉጌታ ዘውዴ - በሱዳን ካርቱም
አምባሳደር እውነቱ ብላታ - በቤልጂዬም ብራስልስ እንዲሰሩ መመደባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ መግለፁ ይታወሳል።

 

በስላባት ማንአየ