በምእራብ አርሲ ጎርፍ ከ2 ሺህ ሄክታር በላይ የእህል ማሳ ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ የጎርፍ አደጋ 2 ሺህ 490 ሄክታር መሬት ላይ በሚገኝ እህል ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

በወረዳዉ በረዶ ቀላቅሎ የዘነበዉ ከባድ ዝናብ በእንሾካላሂሮ፣ ጋሎ ኢላላ እና ሀራጎ ሌመኒ በተባሉ አካባቢዎች በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በዝናቡ በማሳቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው አባወራዎች 822 ናቸው።

የወረዳዉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አሊዪ ኢሬሳ፥ በዝናብ ወቅት እንዲህ ዓይነት አደጋ በተደጋጋሚ እንደሚከሰት ተናግረዋል።

ይህንን አደጋ በተወሰነ መጠን ለመቀነስ የዉሃ መዉረጃ ቦይ መስራት ያስፈልጋልም ነዉ ያሉት።

የዉሃ መዉረጃ ቦዮችን ማሰራት ከወረዳዉ አቅም በላይ ነዉ ያሉት አቶ አሊዪ፥ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ ሊያበጅለት ይገባል ሲሉም አሳስቧል።

በበቂላ ቱፋ