በኦሮሚያ ክልል የበጎ አድራጎት ስራ አመቱን ሙሉ እንዲከናወን ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በክረምት ወቅት ብቻ ተገድቦ የነበረው የበጎ አድራጎት ስራ አመቱን ሙሉ እንዲከናወን ተወሰነ፡፡

የበጎ አድራጎት ስራው በክልሉ በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ በሚገኘው በኦሮሚያ ልማት ማህበር እንዲመራም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ 

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ በሚሊኒዬም አዳራሽ የኦሮሚያ ልማት ማህበር በጎ ፍቃደኞች ቀን በተከበረበት ወቅት፥ የክልሉ ህዝብ ያለውን እውቀት፣ ልምድ እና ጉልበት ጥቅም ላይ ለማዋል የበጎ አድራጎት ስራ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በጎ ፍቃደኝነት የኦሮሞ ህዝብ የቆየ መገለጫ ነው ያሉት አቶ ለማ፥ የህዝቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑንም አንስተዋል።

ይህ ተግባርም በወቅት ሳይገደብ አመቱን ሙሉ ሊተገበር እንደሚገባውም ተናግረዋል።

በበዓሉ ላይ የክልሉ ተወላጆች፣ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናት መገኘታቸውን ባልደረባችን ገመቺስ ምህረቴ ዘግቧል።