የኢራን ፓርላማ የሃገሪቱን የሚሳኤል ፕሮግራም መደገፍ የሚያስችል ተጨማሪ ገንዘብ አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2009 (ኤፍቢሲ) የኢራን ፓርላማ የሃገሪቱን የሚሳኤል ፕሮግራም መደገፍ የሚያስችል ተጨማሪ የ520 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ አፀደቀ።

ከ244 የሃገሪቱ ህግ አውጭዎች የ240ውን ድጋፍ ያገኘው ገንዘብ፥ ቴህራን ለምታካሂደው የሚሳኤል ፕሮግራም ማሳደጊያ ይውላል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ለሃገሪቱ አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ ማጠናከሪያ እንደሚውልም ተገልጿል።

ይህም ኢራን አሜሪካ ትፈጽመዋለች የምትለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመከላከልና በዋሽንግተን ማዕቀብ ኢላማ የተደረጉ አካላትን ለመደገፍ ያስችላታል ነው የተባለው።

ኢራን በሚሳኤል ፕሮግራሟ ላይ ከአሜሪካ ተጨማሪ ማዕቀብ በተጣለባት ወቅት ተጨማሪ ወጪው መጽደቁ ግን የሁለቱን ሃገራት ውጥረት እንዳያባብሰው ተሰግቷል።

የአሁኑ የፓርላማ አባላት ውሳኔም ቴህራን ከአሜሪካ ለተጣለባት ማዕቀብ ምላሽ ሳይሆን እንደማይቀር እየተነገረ ነው።

 

 

ምንጭ፦ ፕረስ ቴሌቪዥን