አየር መንገዱ በአገር ውስጥ በረራዎች ላይ የ40 በመቶ ቅናሽ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቱሪስት ፍሰትን ለመጨመር በሀገር ውስጥ በረራዎች የትኬት ዋጋ ላይ የ40 በመቶ ቅናሽ አደረገ ።


በዘርፉ ያሉ ችግሮችን እና ከቱሪዝም የሚገኝውን ገቢ ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ የሚመለከታቸው  ባለድርሻ አካላት ዛሬ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም  በመግለጫው ላይ እንዳሉት ፤ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ላይ የበረራ መስመር በመክፈት እና የዋጋ ማስተካከያ በማድረግ የቱሪስት ፍሰቱን መጨመር መቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚዎች ማህበር በበኩሉ ከዘርፉ የሚገኝውን ገቢ ለማሳደግና የቱሪስቱን እርካታ ለመጨመር የ20 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ከማድረጉም በተጨማሪ ለአስጎብኚ ግለሰቦች ልዩ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጿል ።

በሆቴሎች አካባቢ ያለው የወጥነት ችግርም እንዲቀረፍ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነው ባለድርሻ አካላቱ የተናገሩት።

በትዕግስት ስለሺ