ትራምፕ የቀድሞ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪቸው እና ሩሲያን በተመለከተ ምርመራ እንዲቋረጥ ኤፍቢአይን ጠይቀዋል -ሪፖርት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀድም የብሄራዊ ደህንነት አማካሪያቸው እና በሩሲያ ያለውን ግንኙነት ምርመራ እንዳይካሄድ የፌደራል የምርመራ ቢሮ ዳይሬክተር የነበሩትን ጄምስ ኮሜንን መጠየቃቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ናቸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው የካቲት ለቀድሞ ኤፍቢአይ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሜ በጻፉት ማስታወሻ “ይህንን ልትተወው እንደምትችል ተስፋ አደርገለሁ “ ማለታቸው ነው የተነገረው፡፡

በፕሬዚዳንቱ የተጻፈው ይህ ደብዳቤ ፥የፕሬዚዳንቱ ቀድሞ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክል ፍሊን ስራቸውን በለቀቁ ማግስት ነው ተብሏል፡፡

ዋይት ሀውስ ክሱን በተመለከተ አስተባብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ጄነራል ማይክል ፈሊንን በተመለከተ ኮሜንን ይሁን ማንንም አካል ምርመራ እንዲቋረጥ አለመጠየቃቸውን ነው ዋይት ሃውስ ያስታወቀው፡፡

አንድ ተጽኖ ፈጣሪ የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤቱ አባል የኤፍቤአይ በአንድ ሳምንት ውስጥ ማናቸውም አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲቀርብ ጠይቀዋል፡፡

የምክር ቤቱ የቁጥጥር ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ጃሰን ቼፌዝ ኤፍቢአይ በኮሜን እና በፕሬዚዳንቱ መካከል የተካሄዱ ሁሉንም የደብዳቤ ልውውጦች እና መረጃዎች ለምክር ቤቱ እንዲያቀርብ አሳስበዋል፡፡


ምንጭ ፦ቢቢሲ


በእስክንድር ከበደ