የኮሪያ ዘማቾች የማህበረሰብ ማዕከል በአዲስ አበባ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 13 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ የኮሪያ ዘማቾች የማህበረሰብ ማዕከል በአዲስ አበባ ልትከፍት መሆኑን አስታወቀች።

ማዕከሉን ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነትም የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርሟል።

የደቡብ ኮሪያ መንግስት የበጎ አድራጎት አገልግሎት ተቋሙን ለመክፈት የሚያስችለውን ስምምነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ነው የተፈራረመው።

የማዕከሉ መገንባት ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ወዳጅነት ማሳያ ከሆኑ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ከ19 50 እስከ 53 ድረስ በተካሄደው የሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት፥ ወደ ደቡብ ኮሪያ ወታደር የላከች ብቸኛ አፍሪካዊ ሃገር ናት።

በወቅቱ 3 ሺህ 5 መቶ ወታደሮች ወደ ኮሪያ የዘመቱ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 650 የሚሆኑት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።


ምንጭ፦ Yonhap