የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ሸሪፍና ቤተሰባቸው የሙስና ወንጀል ላይ ተጨማሪ ምርመራ አዘዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍን ከስልጣናቸው ለማንሳት የሚያስችል በቂ የሙስና ወንጀል ማስረጃ እንዳልቀረበለት ገለጸ፡፡

ፍርድ ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሙስና ወንጀል ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል በፓናማ ፔፐር የቀረበባቸውን ውንጀላ ለማየት ዛሬ ችሎት ከፍቶ ነበር፡፡

በችሎቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ሸሪፍን ወንጀለኛ ለማድረግ እና ከስልጣናቸው ለማንሳት የሚያስችል በቂ ማስረጃ እንደለሌ ጠቅሷል፡፡

በምትኩም በፓናማ ፔፐር በተጠቀሰው ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተጠናከረ ምርመራ እንዲደረግ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

ፓናማ ፔፐር በ2015 በለቀቀው መረጃ ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተሰቦች በተለይም ሶስት ልጆቻቸው በገንዘብ ስወራ ህገወጥ ተግባር አሉበት ብሎ ነበር፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በቤተሰቦቻቸው የቢዝነስ እንቅስቃሴ ላይ በርካታ የውንጀላ ጥያቄዎች ቢነሱም ሸሪፍ ተቃውመውታል፡፡

ስልጣናቸውን ተጠቅመው ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲሰውሩ አድርገዋል የሚለውን ወቀሳም አጣጥለውታል፡፡

ይህ ውዝግብ የፈጠረው ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የወደፊት የስልጣን ቆይታ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፡፡

በኢዝስማባድም በርካታ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ " ናዋዝ ይውረዱ!… ናዋዝ ይውረዱ!" የሚሉ ድምጾችን ሲያሙ ውለዋል፡፡

ሰልፈኞችን ለመበተንም 1 ሺህ 500 ፖሊሶች በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተሰማርተው ነበር ተብሏል፡፡

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፡- ቢቢሲ