ጥቂት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የዛሬ ስድስት አመት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በጋለ ህዝባዊ ተሳትፎ እየተገነባ ይገኛል።

የፊታችን እሁድ መጋቢት 24 ቀን ደግሞ ግድቡ፥ በሚገነባበት የጉባ ወረዳ የተጀመረበት ስድስተኛ አመት ይከበራል።

ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም እየገነቡት ያለው የህዳሴ ግድብ ቁጥራዊ መረጃዎች ይህን ይመስላሉ፤

ግድቡ የሚገኝበት ቦታ - በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጉባ ወረዳ

ግንባታው የተበሰረበት ቀን - መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም

የግድቡን ግንባታ የሚያከናውነው ሥራ ተቋራጭ - የጣሊያኑ ሳሊኒ ኢምፕሬጂሎ

የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎችን የሚያከናውነው - የኢትዮጵያ ብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን

የሚያመነጨው የሃይል መጠን - 6 ሺህ 450 ሜጋ ዋት

ለመገንባት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን - 80 ቢሊየን ብር (ከ4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ)

የሃይል ማመንጫ ዩኒቶች ብዛት - 16

እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የሃይል መጠን - ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት

የዋናው ግድብ ከፍታ - 145 ሜትር

የዋናው ግድብ ርዝመት - 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር

የዋናው ግድብ ውፍረት - የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር

ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን - 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር

ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት - 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር

ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር

የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ከፍታ- 50 ሜትር

የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ርዝመት 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር

በግድቡ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ሰራተኞች ብዛት 10 ሺህ 672

በግንባታ ላይ እየተሳተፉ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች ብዛት - ከ32 ሀገራት የተውጣጡ 450 ሰዎች

ለግድቡ ግንባታ ከህዝብ ቃል የተገባ የገንዘብ መጠን - 12 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር

ቃል ከተገባው እስካሁን የተሰበሰበ ገንዘብ ብዛት - 9 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር

ግድቡን የጎበኙ ኢትዮጵያውያን ብዛት - 250 ሺህ

ግድቡን የጎበኙ የውጭ ሚዲያዎች ብዛት - 400

የግድቡ ግንባታ የደረሰበት ደረጃ በመቶኛ - ከ56 በመቶ በላይ

ምንጭ፦ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት