የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊዎች በሩሲያ መረጃ ጠለፋ ዙሪያ ለህግ አውጪው አካል ማስረጃ ሊያቀርቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል የምርመራ ቢሮ(ኤፍ ቢ አይ) እና የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ማዕከል(ናሳ) ኃላፊዎች በሩሲያ እና በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ዘመቻ ግንኙነት በተመለከተ ለሀገሪቱ ህግ አውጪ አካል ማስረጃዎችን እንደሚያቀርቡ ተሰማ፡፡

የኤፍ ቢ አይ ዳይሬክተር ጀምስ ኮሚ እና የናሳ ኃላፊው አድሚራል ማይክ ሮጀርስ ለመጀመሪያ ጊዜ ባልተለመደ መልኩ ለኮሚቴው በግልጽ ጉዳዩን አስመልክተው ንግግር ያደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኃላፊዎች ትራምፕ ስልኬ በባራክ ኦባማ እንዲጠለፍ ተደርጎ ነበር የሚለውን ስሞታቸውን በተመለከተም ለደህንነት ኮሚቴው ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

ሩሲያ የአሜሪካንን ምርጫ ላይ ተጽኖ ፈጥራለች መባሉን በተደጋጋሚ ያስተባበለች ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በበኩላቸው ጉዳዩን በተመለከተ የሚደረገው ምርመራ ፋይዳ ቢስ መሆኑን ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡

ባለፈው ጥር ወር በክሬምሊን የሚደገፉ መረጃ ጠላፊዎች  የዴሞክራት ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎችን የኢሜል  አድራሻዎች  የሚስጥር ማለፊያ ቃላትን በመስበር መሪዎቹን ሚያስገምቱ መረጃዎችን እንዲያፈተልኩ በማድረግ ትራምፕ ሂላሪን እንዲያሸንፉ አድርገዋል በሚል የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ተቋማት ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ ፦ቢቢሲ

 

ተተርጉሞ የተጫነው፦በእስክንድር ከበደ