የፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ባለቤትና ቤተሰቦቻቸው በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ባለቤት እና ቤተሰቦቻቸው፣ የተለያዩ ክልሎችና ተቋማት በቆሼ አካባቢ በደረሰው አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በዛሬው ዕለት ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በዛሬው ዕለት የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ባለቤት እና ቤተሰቦቻቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የደቡብ ክልል በበኩሉ 5 ሚሊየን ብር በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር 1 ሚሊየን ብር በገንዘብ እና 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቁሳቁስ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ለግሷል፡፡

የብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ 1 ሚሊየን ብር ሲሰጥ፥ የሀረሪ ክልል በ8989 የሁለት ቀን አጭር የፅሁፍ መልዕክት የተሰበሰበ 504 ሺህ ብር ደግፏል፤ የኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሰልጣኝ አመራሮች በበኩላቸው 40 ሺህ 381 ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ዘ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ በሚባለው ስፍራ በአፈር መድርመስ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ለማቋቋም የሚያግዝ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

 

በደመቀ ጌታቸው