ግብፅ የመጀመሪያዋን ሴት አገረ ገዢ ሾመች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ)ግብጽ በናይል ዴልታ ግዛት ናዲያ አህመድ አብዱን የመጀመሪያዋ የሴት አገረ ገዢ አድርጋ መሾሟ ተነገረ ፡፡

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ዘጠኝ ሚኒስትሮችን እና አምስት አገረ-ገዢዎችን ሹም ሽር ያደረጉ ሲሆን ፤ ከስልጣን በተነሱ ባለሥልጣናት ምትክ አዳዲስ የካቢኔ አባላትን ሾመዋል፡፡

የግብርና ፣የፓርላማ ጉዳዮች ፣የአካባቢ ልማት ፣የትምህርት ፣የአስተዳደር ማሻሻያ ና የትራንስፖርት ዘርፎች ሹም ሽር ከተካሄደባቸው ሚኒስትሮች መካከል ይገኙበታል፡:

ግብጽ በ21 አስተዳደራዊ ግዛቶች የተከፋፈለች ሲሆን ፥ ግዛቶቹ የመጀመሪያ የመንግስት አስተዳደር እርከን ናቸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሰሜናዊ ግብጽ የሚገኘው በናይል ዴልታ የቤሃሪያ ግዛት አገረ ገዢ ሆነው እንዲያስተዳደሩ ናዲያ አህመድ አብዱን ሾመዋል ፡፡

ናድያ ከአሌክሳንደሪያ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስ ና ኬሚስትሪ ፋኩልቲ እ.ኤ.አ በ1965 ዓ.ም የተመረቁ ናቸው፡፡

አገረ ገዢዋ የአረብ ሀገራት ውሃ አጠቃቀም ማህበር መሰራች እና የአለም ውሃ ጠቅላላ ጉባኤ አባል መሆናቸው ተዘግቧል፡:

ምንጭ፦http://english.ahram.org.eg/

ተተርጉሞ የተጫነው ፦በእስክንድር ከበደ