ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው መድሃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች ተወገዱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የኮንትሮባንድ ምርቶች አስወገደ።

ምርቶቹ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ናቸው።

የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ የቤተ ሙከራ ኬሚካሎች፣ የጽዳትና ውበት መጠበቂያ ምርቶችና 397 ነጥብ 6 ቶን የተለያዩ ምግቦች ይገኙበታል።

ምርቶቹ ባለፉት ስድስት ወራት የተያዙ መሆናቸውንም ባለስልጣኑ ገልጿል።

ከህገ-ወጥ ምርቶቹ ጋር በተያያዘ ለ13 የምግብ አምራቾች፣ 8 የምግብ አስመጭና አከፋፋዮች እንዲሁም የጤና ተቋማት የጽሑፍ ማስጠንቀቂ የመስጠት፣ ድርጅቶቻቸውን የማሸግ፣ የማገድና ፈቃድ የመሰረዝ እርምጃ መውሰዱንም ነው ባለስልጣኑ የገለጸው።