በባግዳድ በተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ 48 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከባግዳድ የወጡ የህክምና እና የደህነነት መረጃዎች እንደሚሳዩት በባግዳድ ዛሬ በደረሰው የቦብ ጥቃት በትንሹ 48 ሰዎች ሞተዋል፡፡

ቦምብ የተጠመደበት ተሸከርካሪ በከተማዋ ደቡባዊ የባያ አካባቢ ሲደርስ ፍንዳታው የተከሰተ ሲሆን ከ55 በላይ ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል፡፡

በዚሁ ሳምንት ረቡዕ በተፈፀመ ሌላ የቦምብ ጥቃት ከ15 የማያንሱ ሰዎች የሞቱ ሲሆን አራት ሰዎች ደግሞ ማክሰኞ እለት በተመሳሳይ ጥቃት ሞተዋል፡፡

የዛሬውን ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አይኤስ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡

ምንጭ፡-ሬውተርስ