በጀርመን በ2016 ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በእጅጉ መቀነሱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጀርመን በ2016 ጥገኝነት የጠየቁት ሰዎች ቁጥር ከ2015 ጋር ሲነፃፀር በ600 ሺህ መቀነሱ ተሰምቷል።

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ አመት መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በምታስተዳድራት ሀገር ጥገኝነት የጠየቁ ሰዎች ቁጥር 280 ሺህ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

በ2015 የጥገኝነት ጠያቂዎች አሃዝ 890 ሺህ ደርሶ እንደነበርም ነው መረጃዎች ያመለከቱት።

የጀርመን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ፥ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር የቀነሰው በስደተኞች ጉዳይ ላይ ከአውሮፓ ህብረት እና ከቱርክ ጋር በተደረሰው ስምምነት እና በባልካን ሀገራት መግቢያ በተሰራው የተጠናከረ ጥበቃ መሆኑን ገልጿል፡፡

መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜሪከል ለስደተኞች በራቸውን በጊዜያዊነት ክፍት ማድረጋቸው በ2015 ለነበረው ከፍተኛ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር ተጠቃሽ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ