ግብጽ በከፍተኛ ደረጃ የዋጋ ግሽበት እያጋጠማት መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር ላይ የግብፅ መታዊ የዋጋ ግሽበት 24 ነጥብ 3 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።

ካይሮ የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍን፥ የ12 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት የወሰደቻቸችው እርምጃዎች የዋጋ ግሽበቱን ይበልጥ እንዳናረው ነው የተነገረው።

የግብጽ መንግስት ለዚሁ ብድር ሲል የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

የምግብ ምርቶች የዋጋ ግሽበት ተነጥሎ ሲታይም 29 ነጥብ 3 በመቶ ደርሷል ነው የተባለው።

አይ ኤም ኤፍ ለግብፅ የ12 ቢሊየን ዶላር ብድሩን በህዳር ወር ላይ እንዳፀደቀላት ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ