የቀድሞው የጀርመን ፕሬዚዳንት ሮማን ሄርዞግ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 2 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የጀርመን ፕሬዚዳንት ሮማን ሄርዞግ በ82 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

የመራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ፓርቲ ክርስቲያን ዴሞክራቲክ ዩኒየን አባል የሆኑት የቀድሞ ፕሬዚዳንት፥ የበርሊን ግንብ ፈርሶ ምዕራብና ምስራቅ ጀርመን ከተዋሀዱ በኋላ ሀገሪቱን በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል።

በጊዜውም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ማሻሻያወችን በማምጣት የሚታወቁ ናቸው።

 

 

ምንጭ፦ ሬውተርስ