ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሙስ በምክር ቤቱ ተገኝተው ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 2 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የፊታችን ሀሙስ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምክር ቤቱ አባላት ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የምክር ቤቱ ቆይታ በተለይም መንግስት የጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት የእስካሁኑ ውጤት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀምን የተመለከቱ ጥያቄዎች እና ማብራሪያዎች ሰፊ ትኩረትን ያገኛሉ ተብለው የሚጠበቁ ጉዳዮች ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ነበር በምክር ቤቱ ተገኝተው በአዲስ መልክ ያዋቀሩትን ካቢኒያቸው አዳዲስ አባላትን አቅርበው ያስፀደቁት።

android_ads__.jpg