ዶክተር ቴድሮስ በናይሮቢ በተካሄደው የኢጋድ ልዩ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በናይሮቢ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ ልዩ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳተፉ።

ጉባኤው በተለይም በደቡብ ሱዳን ቀውስ እና በወቅታዊ የሶማሊያ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ በኢጋድ የወቅቱ የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ስዩም መስፍን ሪፖርት ቀርቧል።

ዶክተር ቴድሮስ ለኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታም የሚኒስትሮቹን የስብሰባ ውጤት አብራርተዋል።

ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች በአዲስ አበባ ከተፈራረሙት በተቃራኒው በሰላም ድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ያሳዩት መቀዛቀዝ፥ ከሁለት

ወራት በፊት የተፈረመውን ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆንና በሀገሪቱ ሰላምን ለማስፈን እየተደረገ ያለውን እንውቅቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል።

የሰላም ድርድሩን ለማደናቀፍ የሚሞክር ማንኛውም ፓርቲ ሊወሰድበት የሚችለውን እርምጃም ሚኒስትሮቹ አስቀምጠዋል።