ዜናዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አጀንዳ 2063ን እውን ለማድረግ የመንገዶችን ደህንነት ጠብቆ ማቆየትና አህጉሪቱን በመንገድ የማገናኘት ስራ መከናወን እንዳለበት ተገለጸ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስዊድን መንግሥት በኢትዮጵያ ለስደተኞች አቅም ግንባታ የሚውል 10 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል በ2ኛው ዙር 321 ተጠርጣሪዎችና ፍርደኞች ክሳቸው እንዲቋረጥና በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስኗል።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ቦታው ትቅደም ትምህርት ቤት ጀርባ በሚገኘውና ሾላ ገበያ ዶሮ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሽብር እና በሁከት ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ኮለኔል ደመቀ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች ክሳቸው እንዲቋረጥና ይቅርታ እንዲደረግላቸው በተወሰነው መሰረት ዛሬ ከማረሚያ ቤት ተለቀዋል።