ዜናዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመገንባት ላይ ያለው የመኤሶ-ደወሌ የባቡር ሀዲድ 65 ከመቶ በላይ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዩክሬን ምስራቃዊ ግዛት መንግስት እና ታጣቂዎች የተኩስ አቁም ስምምነት ካደረጉ በኋላ ከ1 ሺህ 300 ዜጎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ህወሓት 40ኛ አመት የምስረታ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር በቂ ዝግጅት እየተደረገ ነው አሉ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ )  በደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተሄደው ርቀት የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ ያለውን ቁርጠኝነት አመልካች ነው አሉ በኢጋድ ዋና አደራዳሪ አምባሳደር ስዩም መስፍን።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የቅበላ መስፈርት ሳያሟሉ ተማሪዎችን ተቀብለው ሲያስተምሩ በተገኙ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።