ዜናዎች (11878)

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢብራሂም ማህላብ የተመረቀዉ የግድቡ 50ኛ አመት ዝክር በካይሮ ኦፔራ አዳራሽ ትናንት ሲከበር ፤ የባህል ሚኒስትሩ  ሳብር አረብ ፣ የመስኖ ሚኒስትሩ ሞሃመድ አብደል ሙታሊብ እና የተለያዩ የሃገሪቱ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናትተገኝተዋል፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ ኢንስትቱዩነት  እንዲያድግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

የአማኑኤል  የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሀገረ አቀፍ ደረጃ በመስኩ ህክምና በመስጠት ብቸኛው ነው።

በዚህም 270 የሚጠጉ ህሙማንን አስተኝቶ እንዲሁም ከ 600 ከፍ የሚሉትን ደግሞ የተመላላሽ የአዕምሮ ህክምና እየሰጠ ነው የሚገኘው።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ዳዊት  አሰፋ ሆስፒታሉ የበለጠ እንዲጠናከር እና የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ረቂቅ አዋጁ የሆስፒታሉን አግልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ስልጠናን ጨምሮ  የምርምር እና የልህቀት ማዕከል እንዲሆን የሚያስችለው ነው።

የሚሰጠውን የአዕምሮ ጤና አገልግሎት አቀናጅቶ የመምራት፤  በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት ብሎም ለህክምናው መሻሻል የሚረዱ ግብአቶችን መፍጠር የሚሉ ተጠቃሾች እንደሆኑም ነው  ዶክተር ዳዊት የጠቀሱት።

 ቀደም ሲል ሆስፒታሉ  የስልጠናና የምርምር ስራዎችን በማካሄዱ ረገድ  ውስንነቶች አሉበት የሚሉት ስራ አስኪያጁ ፥ ይህ ደግሞ ረቂቅ አዋጁ ጸድቆ ስራ ላይ ሲወል መፍትሄ ያገኛል ብለዋል።


ያነጋገርናቸው የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሜዲካል ሰርቪስ ሃላፊ ዶክተር ብርቄ አንበሴ እና የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካለ ኮሌጅ የሆስፒታሉ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር ከተማ ድሪባ ኢንስትተየቱ በአዋጅ ጸድቆ ወደ ተግባር ሲሸጋገር ዘረፈ በዙ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያሰችለው ነው የገለፁት።

ዶክተር ዳዊት ረቂቁን የማዘጋጀቱ ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑና በቀጣይ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደሚላክ አስታውሰዋል።

በአሁን ጊዜ የመጨረሻ ውሳኔ ባያገኝም  አዋጁ ከጸደቀ በኋላ የአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስሙ የኢትዮዽያ አዕምሮ ጤና ኢንስቲተየት ይሆናል ተብሎ ነው የሚታሰበው።

ኢንስቲትዩቱ መቀመጫውን የሚያደርግበት ኮተቤ አካባቢ የሚገኘው የአዲሱ ህንጻ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሊጠናቀቅም የ4 ወራት እድሜ ብቻ ይቀረዋል ነው ያሉት የአማኑኤል ስፔፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ዳዊት አሰፋ።

በጥላሁን ካሳ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ከአንድ ወር በፊት በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የወጡ ቅድመ ውጤቶች በምርጫው የትኛውም እጩ ለአሸናፊነት የሚያበቃውን አብላጫ ደምጽ አለማግኘቱን ጠቁመዋል።

ዛሬ ይፋ የሚደረገው የምርጫ ውጤት ይህንኑ የሚያረጋግጥ ከሆነ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ከፍተኛውን ድምጽ ባገኙ ሁለት እጩዎች መሃከል የሚካሄድ ይሆናል።

ቀድመው በወጡት መረጃዎች መሰረት አብዱላህ አብዱላህ እና አሽራፍ ጋኒ ከሌሎች እጩ ከፍ ያለውን ድምጽ በማግኘት የምርጫውን አሸናፊነት ግምት አግኝተዋል።

ምንጭ ፦ ሮይተርስ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የመንገድ ጥገና ፈንድ አባል ሃገራት ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች።