ዜናዎች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍ እና እውቅና መስጠትን ዓላማ ባደረገው በዛሬው የአዲስ አበባ ሰልፍ ላይ የተፈፀመውን የቦምብ ጥቃት የተለያዩ ወገኖች በማውገዝ ላይ ናቸው።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 16፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው ሰልፍ ላይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያን ያለፈውን ልዩነት፣ ቁርሾና ጥላቻ በመተው በይቅርታና ፍቅር ጊዜውን መሻገር እንደሚገባቸው ተናገሩ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 16፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍ እና እውቅና መስጠትን ዓላማ ያደረገ ደማቅ ሰልፍ ዛሬ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሂዷል።


በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በተሳተፉበት በዚህ ሰልፍ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በመገኘት ንግግር አድርገዋል። 

ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተጨማሪ ከተለያዩ ከተማዎች ዜጎች በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ተገኝተዋል።

በሰልፉ መጨረሻ የቦምብ ፍንዳታ ደርሶ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ከደረሰው አነስተኛ ጉዳት ውጪ ሰልፉ በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታውቋል።

ሰልፉ ከተጠናቀቀም በኋላ የቦምብ ፍንዳታ ደርሶ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ከደረሰው አነስተኛ ጉዳት ውጪ ሰልፉ በሰላም መጠናቀቁን የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ሺዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የሰልፉ ዋና ዓላማ በሀገሪቱ አሁን ላይ የመጣውን ለውጥ በማበረታታት እውቅና መስጠት ነው።

በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያውያን ከጎናቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ያለ ልዩነት የተሳተፉበት ነው።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 15፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሃዋሳና በሲዳማ ዞን የተለያዩ ከተሞች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በተቋቋመ ግብረ ሀይል በግጭቱ የተሳፉ 226 ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለፀ።