ሊዊስ ኤኒሪኬ የስፔን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የቀድሞ የባርሴሌኖ አሰልጣኝ ሊዊስ ኤኒሪኬ የስፔን ብሄራዊ ቡድንን ለማሰልጠን የሁለት ዓመት ኮንትራት ፈረሙ፡፡

የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ዩለን ሎፔቴጉይን ዓለም ዋንጫ ከመድረሱ ከሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ከሃላፊነት ማንሳቱን ይታወሳል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ፥ አሰልጣኝ ሎፔቴጉይ ፌዴሬሽኑን ሳያማክሩ ሪያል ማድሪድን ለማሰልጠን በመስማማታቸው ምክንያትት ከሃላፊነት ለማንሳት መገደዳቸውን መናገራቸውም የሚታወስ ነው።

ሊዊስ ኤኒሪኬ በሦስት ዓመት የባርሴሎና ቆይታቸው ዘጠኝ ታላላቅ ዋንጫዎችን አሸንፈዋል፡፡

ኤኒሪኬ በ2011/12 የውድድር ዓመት ወደ ጣሊያን በማቅናት ሮማን ማሰልጠኑ የሚታወስ ሲሆን ከሀገሩ ስፔን ውጪ ያደረገው የመጀመሪያው ሙከራው ነበር ተብሏል፡፡

ሉዊስ ሩቢያሌስ የ48 ዓመቱ ሊዊስ ኤንሪኬ የስፔን ብሄራዊ ቡድንን ለማሰልጠን ያላቸውን ፍቅር አወድሰዋል፡፡

እንዲሁም ፌዴሬሽኑ የሚልገውን ሁሉንም ቅድመ ሁኔታ የሚያሟሉ አሰልጣኝ ናቸው ብለዋል፡፡

ኤንሪኬ በወጣትነት ዘመናቸው ለሪያል ማድሪድና ለባርሴሎና ተጫውቷል በአሰልጣኝነት ዘመኑም የስፔን ላሊጋ፣ ቻምፕዮንስሊግና ሌሎች ዋንጫዎችን አንስቷል፡፡

ሊዊስ ኤንሪኬ የስፔን ብሄራዊ ቡድንን ይዘው የመጀመሪያ ጨዋታቸውን መስከረም መጀመሪያ ላይ ከእንግሊዝ ጋር ብሄራዊ ቡድን ጋር በዌንብሌ ስታዲየም እንደሚጫወቱ ይጠበቃል፡፡


በአብርሃም ፈቀደ