ፖርቹጋል ሞሮኮን አሸነፈች

አዲስአበባ፣ ሰኔ 13፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩሲያ እየተካሄደ ባለው 21ኛው የዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለት ሁለተኛ ዙር ፖርቹጋል ሞሮኮን አሸነፈች፡፡

ፖርቹጋልና ሞሮኮ 9፡00 ሰዓት ላይ የተገናኙ ሲሆን በመጀመሪያው አጋማሽ በተቆጠረ ጎል ነው ያሸነፈችው፡፤

የፖርቹጋልን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረው ሮናልዶ ሲሆን በሁለት ጨዋታዎች አራት ጎል በማስቆጠር ኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

ከፖርቹጋል አንጻር በኳስ ቁጥጥር የተሻለ ብልጫ የነበራት ሞሮኮ ከዓለም ዋንጫው በመጀመሪያ ዙር የመሰናበት ዕድሏ ሰፊ ነው፡፡

ምድብ አንድ ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ኡራጓይ እና ሳዑዲ አረቢያ 12፡00 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

በምድብ አንድ ትላንት ሩሲያ ግብጽን ማሸነፏ ተከትሎ በስድስት ነጥብ ምድቡን እየመራች ትገኛለች፡፡

እንዲሁም ኡራጓይ በመጀመሪያው ጨዋታዋ ግብጽን 1 ለ 0 መርታቷ የሚታወስ ሲሆን፥ ዛሬ ሳዑዲን የምታሸንፍ ከሆነ ከሩሲያ እኩል ነጥብ ይኖራታል፡፡

ከምድቡ አፍሪካዊቷ ግብጽ ባደረገቻቸው ሁለት ጨዋታዎች ሽፈንት ያስተናገደች ሲሆን፥ ከዓለም ዋንጫ የመሰናበት እድሏም ሰፊ ነው፡፡

 

 

 

 

ምንጭ፥ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ