ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ ፣ 9፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን ሲያሸንፍ ድሬደዋ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ዛሬ በ10 ሰዓት አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ደደቢት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ በፈረሰኞቹ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል።

የቅዱስ ጊዮርጊስን የአሸናፊነት ግቦች ሰልሃዲን በርጌቾ በ3ኛው ደቂቃ፣ ሙሉዓለም መስፍን በ41ኛው ደቂቃ እና ምንተስኖት አዳነ በ63ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችለዋል።

በሌላ ጨዋታ ድሬደዋ ከኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።

እረፋድ ላይ በተካሄዱት ጨዋታዎች ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከነማ ማሸነፍ ችለዋል።

ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ ኦኪኪ አፎላቢ በ37ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት እና አሮን አሞሃ በ67ኛው ደቂቃ ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል።

በሌላኛው ጨዋታ ወጥ አቋም ማሳየት የተሳነው ፋሲል ከነማ አፄ ፋሲለደስ ስታደየም ላይ ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ፋሲል ከነማን አሸናፊ ያደረጉትን ግቦች ራምኬሎክ በ30ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት እና ኤፍሬም አለሙ በ35ኛው ደቂቃ ሲያሰቆጥሩ ሲዳማ ቡና ከሽንፈት ያልታደገችው ግብ ሀብታሙ ሀዛኸኝ አስቆጥሯል።

ይህን ውጤት ተከትሎም ጅማ አባጅፋር በ48 ነጥብ እና በ16 ንፁህ ጎል ፕሪምየር ሊጉን በአንደኝነት መምራት ችሏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በእኩል 48 ነጥብ በ15 ንፁህ የግብ ክፍያ በሁለተኛ ደረጃ ሲይዝ፤ ኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ ከተማ በእኩል በእኩል 43 ነጥብ ተከታዮቹን ደረጃ ይዘዋል።