እንግሊዝ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ የሚወክሏትን ተጫዋቾች ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ለ2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አደረገ።

አሰልጣኙ ክሪስ ስሞሊንግ እና አዳም ላላናን ከቡድኑ ውጭ አድርጓቸዋል።

በአሰልጣኝ ሳውዝጌት ስብስብ የተካተቱት ተጫዋቾች ዝርዝር፤

ግብ ጠባቂ፦ ጃክ በትላንድ (ስቶክ ሲቲ)፣ ጆርዳን ፒክፎርድ (ኤቨርተን) እንዲሁም ኒክ ፖፕ ከበርንሌይ ተመርጠዋል።

ተከላካዮች፦ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ (ሊቨርፑል)፣ ጋሪ ካሂል (ቼልሲ)፣ ካይል ወከር እና ጆን ስቶንስ (ማንቼስተር ሲቲ)፣ ሃሪ ማጉይሪ (ሌሲስተር ሲቲ)፣ ኪዬራን ትሪፐር እና ዳኒሮዝ (ቶተንሃም ሆትስፐርስ) እንዲሁም ፊል ጆንስ እና አሽሊ ያንግ ከማንቼስተር ዩናይትድ ተመርጠዋል።

አማካዮች፦ ኤሪክ ዳዬር እና ዴሊ አሊ (ቶተንሃም ሆትስፐርስ)፣ ጀሴ ሊንጋርድ (ማንቼስተር ዩናይትድ)፣ ጆርዳን ሄንደርሰን (ሊቨርፑል)፣ ፋቢያን ዴልፍ (ማንቼስተር ሲቲ) እንዲሁም ሩበን ሎፍተስ ቼክ ከቼልሲ በቡድኑ ተካተዋል።

አጥቂዎች፦ ጄሚ ቫርዲ (ሌሲስተር ሲቲ)፣ ማርከስ ራሽፎርድ (ማንቼስተር ዩናይትድ)፣ ራሄም ስተርሊንግ (ማንቼስተር ሲቲ)፣ ዳኒ ዌልቤክ (አርሰናል) እንዲሁም ሃሪ ኬን ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ተካተዋል።

ቶም ሂተን፣ ጄምስ ታርኮውስኪ፣ ሊዊስ ኩክ፣ ጃክ ሊቨርሞር እና አዳም ላላና ደግሞ የሚጎዳ ተጫዋች ካለ ለመተካት በተጠባባቂነት ተይዘዋል።


ምንጭ፦ ቢቢሲ