ዘላለም ሽፈራው የወልድያ ከተማ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የወልድያ ስፖርት ክለብ ዋና አሰልጣኝ መሆነው መሾማቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ ከዛሬ ጀምሮ ክለቡን በይፋ ተረክበው ማሰልጠን እንደሚጀምሩም የወልድያ ስፖርት ክለብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ሃዋሳ ከነማ፣ አዳማ ከነማ፣ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከነማ የመሳሰሉ ክለቦችን በማሰልጠን ሰርቷል።

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ወደ ወልድያ መምጣትም ክለቡን ሊያነቃቃው እንደሚችል ተገምቷል።

የወልድያ ስፖርት ክለብ ባሳለፍነው ሳምንት አሰልጣኝ ያዕቆብ አብረሃምን የእግር ኳስ ክለቡ ምክትል አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙም ይታወሳል።

ወልዲያ በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ሲመራ ቢቆይም አሰልጠጣኙ የአንድ ዓመት ቅጣት በመቀጣታቸው ቡድኑ በምክትሉ ኃይማኖት ግርማ እየተመራ መቆየቱ ይታወሳል።