በፕሪምየር ሊጉ አዳማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀናቸው

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ በተከናወኑ የፕሪሚየር ሊጉ ተስተካካይ ጨዋታዎች አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ ሁለተኛ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተገናኝተዋል፡፡

በጨዋታውም ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 የረታ ሲሆን፥ ይህንን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሪምየር ሊግ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡

የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲና የመቐለ ከተማ ጨዋታ የክልሉ ኮማንድ ፖስት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ አልተካሄደም፡፡

ወልዋሎና መቐለ ዛሬ እንዲጫወቱ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም፥ ጨዋታው ዛሬ እንደማይካሄድ የትግራይ ክልል የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ፕሪምየር ሊጉን ጅማ አባ ጅፋር በ22 ጨዋታዎች በ39 ነጥብ በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ21 ጨዋታዎች 36 ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፥ አዳማ ከተማ በ22 ጨዋታዎች በተመሳሳይ ነጥብ በግብ በመለያየት ወደ ሦስተኛ ደረጃ መጥቷል፡፡