በለንደን ማራቶን ቶላ ሹራ 2ኛ ሲወጣ በሴቶች ታደለች በቀለ 3ኛ ወጥታለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ38ኛው የለንደን ማራቶን ማራቶን የሩጫ ውድድር በዛሬው እለት ተካሂዷል።

በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያዊው አትሌት ቶላ ሹራ 2ኛ ሆኖ አጠናቀቀ በሴቶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ አትሌት ታደለች በቀለ 3ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል።

ለየንደን ማራቶን የወንዶች ውድድረን ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾንጌ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ27 ማይርኮ ሰከንድ በማድባት በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ውድድሩን 2ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያዊው አትሌት ቶላ ሹራ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ00 ሰከንድ በማግባት አጠናቋል።

በውድድሩ ላይ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረው እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ደግሞ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በውድድሩ የእንግሊዝን ክብረ ወሰን በማሻሻል እንደቻለም ተነግሯል።

በውድድሩ ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቶት የነበረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2 ሰዓት ከ08 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት 6ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል።

በሴቶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ ኬንያዊቷ አትሌት ቪቪያን ቼሮይት 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች።

ሌላዋ ኬንያዊት አትሌት በሪግድ ኮስጌዪ ሁለተኛ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ታደለች በቀለ ደግሞ 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ30 በመግባት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።

በውድድሩ ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቷት የነበረው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ደግሞ ውድድሩን ማቋረጧ ነው የተነገረው።