በፊፋ ወርሃዊ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ 8 ደረጃዎች ዝቅ አለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፊፋ ወርሃዊ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከነበረችበት በስምንት ደረጃዎች ዝቅ ብላለች።

አለም አቀፉ የእግርኳስ የበላይ አካል /ፊፋ/ የመጋቢት ወር የሃገራት ብሄራዊ ቡድኖች ደረጃን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

በፊፋ ወርሃዊ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ መሰረትም ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከነበረችበት በስምንት ደረጃዎች ዝቅ በማለት ከዓለም 145ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ቱኒዚያ፣ ሴኔጋል እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከአፍሪካ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ጀርመን ያለፈው ወር ደረጃዋን በማስጠበቅ በቀዳሚነት እየመራች ሲሆን፥ ብራዚል፣ ቤልጂየም ፖርቹጋል እና አርጀንቲና በቅደም ተከተላቸው ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በአንፃሩም አንጉሊያ፣ ባህማስ፣ ሶማሊያ፣ ቶንጋና ኤርትራ የመጨረሻው 207ኛ ደረጃ ላይ ናቸው።

ምንጭ፦ www.fifa.com