በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወላይታ ድቻ ዛማሌክን በመርታት ወደ ሶስተኛው ዙር አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የወከለው ወላይታ ድቻ የግብጹን ዛማሌክን በመርታት ወደ ሶስተኛው ዙር አለፈ።

በካይሮ አል-ሰላም ስታዲየም በተካሄደ የመልስ ጨዋታ 90 ደቂቃውን በዛማሌክ  2 ለ 1 መሪነት በመጠናቀቁ ድምር ውጤቱ 3 አቻ በማለቁ የመለያ ምት ተሰጥቶ ዲቻ በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ትላንት በአፍሪካ ቻምፒየስ ሊግ ባደረገው ጨዋታ በኡጋንዳው ኬሲሲኤ 1 ለ 0 በመሸነፉ ከውድድር መሰናበቱ የሚታወስ ነው።