ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ በተለያዩ ጨዋታዎች ይቀጥላል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) 20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተማዎች ይካሄዳል።

ዛሬ 9 ስአት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ፤ 11 ስአት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ የሚደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረት ማግኘት ችሏል።

በክልል ከተሞች ዳሽን ቢራ ከሀዋሳ ከነማ ፣ ሙገር ሲሚንቶ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና  ፣ አርባምንጭ ከነማ ከመብራት ሃይል እንዲሁም ሀረር ከተማ ከወላይታ ዲቻ  በተመሳሳይ 9 ስአት ላይ ይገናኛሉ።

በቶማስ ሰብስቤ