በፕሪሚየር ሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ ወልዲያና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ተካሂዷል።

ከተጫዋቾቹ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት አራት የፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮችን ያላደረገው ወልዲያ ከተማ ዛሬ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫውቶ አንድ አቻ ተለያይቷል።

ዲዲዬ ለብሪ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ አንዷለም ንጉሴ ደግሞ ለወልዲያ ከተማ የአቻነቷን ጎል አስቆጥሯል።

ሊጉን ደደቢት ከ13 ጨዋታ በሰበሰበው 28 ነጥብ ይመራል።

15 ጨዋታ ያደረጉት መቐለ ከተማ እና አዳማ ከተማ ደግሞ በ25 እና 23 ነጥቦች ይከተላሉ።

ድሬዳዋ ከተማ፣ አርባምንጭና ወልዲያ ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።

ጌታነህ ከበደ በ9 ግቦች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን ሲመራ፥ ዳዋ ሁቴሳ፣ ኦኪኪ አፎላቦና አልሃሰን ካሉሻ ደግሞ በ7 ግቦች ይከተላሉ።

በነገው እለት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት 10 ሰዓት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።


ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ