በዩሮፓ ሊግ ኤሲሚላን ከአርሰናል ተገናኝተዋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ ሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል።

በዚህ መሰረት የመጀመሪያ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎቻቸውን በደርሶ መልስ ያሸነፉ ክለቦች እርስ በርስ የሚገናኙ ይሆናል።

የጀርመኑ አር ቢ ሌፕዚግ ከሩሲያው ዜኒት ሲደለደል የጣሊያኒ ላዚዮ ደግሞ ከዳይናሞ ኬቭ ጋር ይጫወታል።

አትሌቲኮ ማድሪድ ሎኮሞቲቭ ሞስኮን ሲያስተናግድ፥ ዶርትመንድ ደግሞ ከኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ ጋር ተደልድሏል።

የእንግሊዙ አርሰናል የመጀመሪያ ጨዋታውን ወደ ሳንሲሮ አቅንቶ ከኤሲ ሚላን ጋር ያደርጋል።

የፈረንሳዩ ማርሴይ ከስፔኑን አትሌቲክ ቢልባኦ፥ ሊዮን ከሩሲያው ሲ ኤስ ኬ ሞስኮም የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ናቸው።

የፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ደግሞ ከቼክ ሪፐብሊኩ ቪክቶሪያ ፕልዘን ጋር የሚጫወት ይሆናል።