ሲቪያ የአውሮፓ ማህበረሰብ ዋንጫን አነሳ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአውሮፓ ማህበረሰብ ዋንጫ የስፔኑ ሲቪያ የፖርቱጋሉን ቤንፊካ በመለያ ምት አሸነፈ።

 

ትናንት ምሽት 3 ከ 45 በጁቬንቱሱ ስታዲየም የተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ መደበኛው 90 ደቂቃ እና ተጨማሪው ሰዓት ያለግብ ተጠናቋል።

በተሰጡ የመለያ ምቶችም ሲቪያ 4 ለ 2 በማሸነፍ በ9 ዓመታት ውስጥ ሶስተኛ ዋንጫውን በእጁ አስገብቷል።

በአንፃሩ ቤንፊካ ለዋንጫ ከደረሰባቸው የአውሮፓ ማህበረሰብ ዋንጫ ጨዋታዎች ስምንቱን በሽንፈት መደምደሙ እያነጋገረ ነው።

በምሽቱ ጨዋታ ጫና ፈጥረው ለመጫወት የሞከሩት ቤንፊካዎች ዕድል ፊቷን አዙራባቸው አምሽታለች።

ቶተንሃምን እና ጁቬንቱስን ከውድድር ዉጪ ያደረገው የጆርጅ ጂሰሱ ቤንፊካ እንደተለመደው ዋንጫ ለመሳም እንደጓጓ አሳዛኝ ተሸናፊ ሆኗል።