በፕሪምየር ሊጉ ቅ.ጊዮርጊስና መቐለ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬ ጎንደር እና አዲስ አበባ ላይ ተደርገዋል።

በዛሬው እለት ቀደም ብሎ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም ተገናኝተው ጨዋታቸውን አድርገዋል።

በጨዋታውም ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን በሜዳው 2ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሃይሉ አሰፋ ጨዋታው በተጀመረ በ1ኛው ደቂቃ እና በአብዱልከሪም ኒኬማ ከዕረፍት መልስ 59ኛ ደቂቃ ላይ ባስቆጠሩት ሁለት ጎሎች ነው ፋሲል ከተማን መርታት የቻሉት።

ዛሬ በተደረገ ሌላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ደግሞ ወልዲያ ከተማ እና ከመቐለ ከተማ አዲስ አበባ ላይ አገናኝቷል።

ጨዋታውም በመቐለ ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የመቀሌ ከተማን የማሸነፊያ ጎል አንተነህ ገብረክርስቶስ በ33ኛ ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።