በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

በዛሬ እለትም አንድ የ6ኛ ሳምንት ጨዋታ የተካሄደ ሲሆን፥ በጫወታውም ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ሲዳማ ቡናን 3 ለ 0 ውጤት አሸንፈዋል።

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህይወት ደንጊሳ፣ አይናለም አሳምነው እና ረሂማ ዘርጋ እያንዳንዳቸው በድምሩ 3 ግቦችን አስቆጥረዋል።

ትናንት በተደረገው የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መከላከያ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

 

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ